የቀደመው ዘመን እና አጼ ዘርአ ያዕቆብ፦ ከ600 ዓመታት በፊት የነበሩት አጼ ዘርአ ያዕቆብ እውቀትን ለማስፋፋት፣ መጻሕፍት እንዲተረጎሙ፣ የመጀመሪያው የቤተ-መጻሕፍት መደብ (Library) እንዲቋቋምና የአደባባይ ትምህርት እንዲሰጥ በማድረግ ረገድ የነበራቸውን ቀዳሚ ሚና ዶክተር አንዱዓለም ያብራራሉ::
በአድዋ ጦርነት ወቅት የአዝማሪዎች (እንደ አዝማሪ ጣዲን) ህዝብን የመቀስቀስ ሚና እንዲሁም ከጣሊያን ወረራ በኋላ እንደ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ እና ከበደ ሚካኤል ያሉ ታላላቅ ደራሲያን ማኅበረሰቡን በስነ-ጽሑፍ ለመቅረጽ ያደረጉት አስተዋጽኦ ይነሳል::
የደርግ መንግሥት ኪነጥበብን (በተለይ አብዮታዊ እና ሀገራዊ ዘፈኖችን፣ የሹፌሮች መዝሙርን ወዘተ) ለፖለቲካዊ ዓላማውና ለአብዮቱ ማስቀጠያነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጠቀመበት ይገለጻል። በተመሳሳይ ኢሕአዴግም ጥበብን ከጠመንጃ እኩል ለታጋዮች ሞራል ግንባታ ተጠቅሞበታል ::
አሁንም ድረስ በሰፊው የሚታወቀው «ተነሳ ተራመድ» የተሰኘው መዝሙር፣ በመጀመሪያ በንጉሡ ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ በታሰሩ የአየር ኃይል አባላት የተጻፈና የተቀመረ እንደነበር፣ በኋላ ግን ደርግ ወስዶ በሰፊው እንደተጠቀመበት ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታን ዋቢ በማድረግ ተገልጿል
#Ahadutv #Ahaduradio #Ethiopia #አሐዱቲቪ
AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the media industry by producing strong political, social, and economic contents, which evolve from a secondary to an essential news source, with dozens of bureaus and freelancer around the world and the nation. AHADU features live coverage of the top stories of the day and deep dives into key issues facing the nation and the world.
On-air and online, present’s fact-based, independent journalism that examines and airs diverse perspectives. Our journalists strive for mastery of the narrative form, telling stories in ways that transport the audience to the places where news is happening and introducing the people affected and bringing about tangible results and impact.
Comments
Sign in to leave a comment.